Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መጩገ ደጅም በቭወሰጅ ስሱሞገ ሹምዩ መኮገገ ስዲስ አበባ ጥር ወ ሰሎሞኘ ሹምዩ የደራሲው መብት በሕገ የተጠበቀ ነው። ሄደች የማርያም ወዳጅ ዞራም አላየች ልጅ ውላጅ ይብሳኝ እንጂ እኔ ለራሴ ለሚረበሸው መንፈሴ ለእርሷማ አለቻት ወዳጂ ሁሉ በጂ ነው በደጂ ሰምሮልኝ ልፋት ጥረቴ ደስታ ሲያሰክረው ስሜቴ ወደ ቤት እንመለስ እንዳለቻት ፈጠነ ግን እንደተከተሳቸው። አለ ዶክተር ከፊቱ ቀድሞ በሩን እየያዘ እንዳለ በመሄዱ ከፀና ዶክተር በቀላሉ ስለማይለቀው ለማሳመን ብዙ መቀበጣጠር ሊኖርበት ነው መናገር ደግሞ አልፈለገምተመልሶ ተቀመጠ ዱዳ የሆነ እስኪመስለው ዝምታ ተጭኖታል ዶክተር ስሜቱ ስለገባው ከዚያ ወዲያ ሊያነጋግረው አልሞከረም ከምሳ በኋላ ወይንም ሲሸኝው መኪና ውስጥ ካልሆነም ሌላ ጊዜ ያነጋግረዋል። አለና ራሱን ጠየቀ ዶክተር በማን ነው የተናደደው። መልሱን መቼም ይሁን መቼ ከራሱ ከእንዳለ አንደበት እና ሁኔታ ያገኘዋል ባጠቃላይ ሁኔታው ግን አዘነ። ላፈቀረ ትንሽ ይበቃዋል ከምንወደው ከምናፈቅረው ብዙ እንጠብቃለን ትንሽ ስናጣ ሁሉን እንዳልነበር እናበላሻለን ፍቅር ብሎ ነገር። አሁንም ፍርሃት ፍርሃት ድንግጥ ድንግጥ ያደርጋቸዋል በእንቅልፍ ልባቸው መቃዥቱንም አልተዉም ፈለቸውን መቆጣጠር እንደጀመሩ ከሚደረግላቸው የመድሃኒት ገብረወ ጾ አንድ ምክር ከልባቸው ገብቷል አድ በየኒዚው ደጋግመው የሚሰግሏቸው ዶክተር ገብረወልድ ሲነግሯቸው የሰጧቸው ማሳሰቢያ አለ። እርሷ ያየችው ከእርሱ በቀር ወንድ አለማወቋን ነው መተማመናቸውን ተማምናም ነው አለቀኑ የመጣባትን እርግዝና ሳትደብቅ የነገረችው ቢያምናት ምን ነበረበት። አራት ኪሎ ነዳጅ ማደያ አብረውት የሚሠሩ ጓደኞቹንና ሌሎችንም ሰዎች ሰብስቦ እያመጣ በመጋበዝ ገበያዋን አሟሟቀላት ክቀን ወደ ቀን ፊቷ እየተፈታለትና እየተግባቡ መጡ ጠላ በሌለበትም ቀን ጐራ ብሎ አጫውቷትና ሰላም ብሏት መሄድ ጀመረ ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ እርሷ የምትሰጋውና የምትፈራው ጉዳይ ነበር የፍቅርም ሆነ የጋብቻ ጥያቄ እንዳያነሳባት የፈራችው አልቀረም አንድ ቀን ጠላ በሊለበት መጣና እንደወትሮ ካጫወታት በኋላ እንደሚያፈቅራት አነሳባት ሲያፈቅራትም ለዕለት የሥጋ ፍሳጐት ሳይሆን ለዘላቂ የትዳር ዓላማና ለቁም ነገር መሆኑን ገለፀላት እርሷ ግን ጥያቄውን ልታሟላ የማትችልበት ምክንያት እንዳሳት ገልፃ ፈቃዷን ነፈገችው ባንድ ቀን አልተረታም ደጋግሞ ወተወታት እርሷም ልታሳርፈው ብላ ከሌላ ያረገዘችውና አባት የሌለው የሦስት ወር ቅሪት እንዳላት ፍርጥ አድርጋ ነገረችው የሚያግደው አልሆነም እንጂ። ከዚያማ አንቺ ተፈጠርሽ አሉ ፍርጥ አድርገው ምን። አለች በጥፊ እንደተመታ ሰው ጆሮ ግንዷሏ እየነደደ ምን። ደግሞ ደጋግሞ ጥያቄዋ ለራሷ ደወለባት በህሊናዋ እና አባቴ ማን ነው ልትይኝ ነው። በቀጾ ህክምና ዘዴ ወገጾችን ማምከገ ሂላጻጀርፕዐእነን መወገጾች ተጨማረ ዕሰጅ ሳሰመፈሰጋቸው ከርግጠኛ ሲሆኑ ሀሚገሰገሱ ብ ዘሰቄታዊ የክከርገዝና መከሳከያ ዘጻ ነው።
ይኹ ታዲያ ምንድነው። ዛሬ ቀን። አለች በልቧ በቀላሉ መታለላቸው ለሷ ካላቸው ጥልቅ ፍቅር እና እምነት የመነጨ መሆኑን አስባ ለምን በሰዓቱ እንዳመካኘች ግን ከነከናት ጠፋ ያለቻቸውን አዲስ ሴኮ ፋይቭ ሰዓት ከዝላት ሦስት ወር እንኳን አይሞላውም ያለፈው እሁድ የእርሷና የእንዳለ ነፃ እሁድ ፍሪ ሰንደይ ነበር ሲላፉ እንደቆዩ እንደዋዛ ከእጂ ሳይ የተፈታውን ስዓት አውልቆ ራሱ እጅ ላይ አሰረው እንዲመልስ አልጠየቀችውም ረስታው ሳይሆን ፈቅዳው ይልቁንም የርሷን ሰዓት በማሠሩ ተደስታፎ የእርሱን ደግሞ እርሷ ብታስር ደስ የሚላት ቢሆንም ሠሪ ቤት ስለስጠው አላስረም ነበር ሲለያዩ ያንተ እስኪሠራ ተጠቀምበት አለችው እንዳለ ከወደደላት እንኳን ሰዓቷን ነፍሷን አውጥታ ብትሰጠው አያረካትም ትወደዋለቻ ይሁን እንጂ ስጦታ እንዳልስጠችውና መመለሱም እንደማይቀር ታውቃለች ታዲያ ለምን ለእናቷ መጥፋቱን ዋሸቻቸው። ዳርምየለሽ የለችም እንዴ። ተጠያይቆ ከትምህር ቤቷ እስከ ሰፈሯ የሚያውቃት ሁሉ ቢገረምና ቢቆጭም እርሷ ግን ሥራዋን ስለምታውቅዕለቱን አልቅሳ እንዳለን አያሳጣኝ ብላ ተጽናናች ይልቁንም ቀድሞውኑ የነበራትን የመጻሕፍት ፍቅር ከእንዳለ ፍቅር ጋር አጠናክራ ያዘችው ፍላጐቷን የተገነዘበው እንዳለም እንግሊዝኛ መጻሕፍትን ሳይቀር ቀለል ካለ ወደ ከባድ የቋንቋ ደረጃ እያለማመደ ማቅረቡን ተያያዘውፅ እርሷም በተለይ ከፍቅር ልቦለዶች ጥሩ ጥሩዎቹን በራሷና በእንዳለ እየመሰለች የዝ ባህሪያቱ ታሪክና የፍቅራቸው ስኬ ት በደስታ ሲያሰክራትመጥፎ መጥፎው ደግሞ ሲያሸማቅቃትና ሲያስለቅሳት ፍቅሯ ነዶ የማያልቅ ጣፋጭ ነበልባል ሆነ እንዳለም በበኩሉ ከእርሷ ባላነሰ ሁኔታ እሚይዝ እሚጨብጠውን እስኪያጣ በፍቅር ከነፈ ይሁን እንጂ ከዳርምየለሽ በስድስት እንቁጣጣሽ ቀደም ያለ ዕድሜውና ተወልዶ ያደገበት የችግር ህይወት ባጐናጸፈው ብስለት ታግዞ ሥራውን ጠንቅቆ ከመሥራት አልተደናቀፈም እንዲያውም በፕሬስ መምሪያ ኮንትራት የተቀጠረው ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባህል ዓምድ ረዳት አዘጋጅነት ሲሆን ከአሥር ወር በኋላ የዓምዱ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ሥራውን ለቆ በመውጣቱ እንዳለ ቦታውን ሸፍኖ እንዲሠራ በቋሚነት ተመደበ ማታ ከእርሷ ተለይቶ ሲሄድ ያለፈቃዱ ሊታሠርበት የሚሄድ ያህል ቤቱን እንዲጠላውና እንዲፈራው ጧትም ሥራ ሲገባ ሰላሳ ዓመት በእሥር ቆይቶ ዛሬ ትፈታለህ እንዳሉት አስረኛ ከሥራ የመውጫውን ሰዓት በተሰፋና በጉጉት እያሰላ እንዲናፍቅ አድርገው ሲያቅበጠብጡት የነበሩ ግንፍል የፍቅር ቀናት ሳምንታትና ወራት በርካታ ነበሩ አንድ ሰሞን ታዲያ ከየቀኑ መተያየት ሌላ በተከታታይ የተለቀቁበት ፍሪ ሰንደይ ከበስተኋላው የፀረነፃነት መዘዙን ጥሉባቸው አለፈ ሳያዛንፍ ያዘንብ የነበረው የሲትነት ተፈጥሮዋ ወርሃዊ ደመና እንዳንዣበበ ቀረ ሰሱሞኘ ሹምዩ ዳርምየለሽ ብቻዋን ተጨንቃና ተጠብባ የሁለተኛ ወሯን መጀመሪያ አሥራ እምስት ቀን ስትጨርስ የማይቀር ነውና ነገረችው ማርገዚን በህኪም ካረጋገጡ በኋላ ተሯሩጠው ማንም ሳያውቅ የሁለት ወር ቅሪቷን አስወገደች ከዚያ በኋላ ሁሉም ዕሁድ እንሄገኙየሚዘሉበት አልሆነም ከደረሰባቸው ተምረው በመከላከያው ላይ ተመካከሩ ከብዙ ውይይትና አማራጭ ፍለጋ በኋላም እንዳለ መጻህፍትን አገላብጦ ባገኘው መፍትሔ ላይ ተሰማሙ ነፃው ዕሁድ እስኪደርስላቸው አንዳቸው የአንዳቸውን ገላ እየናፈቁ ቀናቱን መቁጠር እንጂ በመሐሉ የሚያሰቸግር የለም ዝናብነው ፀሐይ ሰሞኑን። በል ልቀቀኝ አለችና በእልህ መንጭቃው ሮጠች በብሽቀት እያጥላላትና እየተሳደበ ቀረ በማግስቱ በዚያው ሰዓት በዚያው ቦታ ሀብታሙ ሳይሆን ያ በርቀት ሲመለከታቸው የነበረ ጓደኛው ብቻውን ቆሞ ጠበቃት የጐንዮሽ አይታው እንዳላየ ዘግታው አለፈች እርሱም ምንም አላላት በማግስቱም ለሁለተኛ ጊዜ ብቻውን ቆሞ ጠበቃት አሁን ካሁን ይለክፈኛል ብላ እንደጓደኛው አልፈልግም በማለት ልታሳፍረው ተዘጋጀች እንዴት ተኮሳትራ እንዴት እንደምትሰድበው ከዚያም አንዴት እንደምታመልጠው ስታስብ ቃል ሳይተነፍስ በማየት ብቻ ቆሞ አሳለፋት በተመሳሳይ ሁኔታ ምንም ምንም ሳይላት በዓይን ብቻ ተቀብሎ እየሸኛት ሁለት ወራት አለፉ በዚያ ሁለት ወር ጊዜም እያደር ላይታወቃት ከትምህርት ቤት እንደወጣች ቅድስት ማርያም አጠገብ ዓይኗ የለመደውን አንድ ነገር ማየቷ እንዳይታወቅባት በጥንቃቄ ሠረቅ አድርጋ መፈለግ ጀምራለች ቀጠን ብሎ እጅግም ባልረዘመና አጭርም በማይባል መጠን የተዋቀረ ቁመና ያለው ሳላ ቀላ ያለው ፀጉሩ ከወደ ግንባሩ ወደፊት ቀደም ያለ ቀይ ጥቁር ወይንም ጠይም ለማለት የሚያስቸግርነገር ግን በጠይምና በቀይ ዳማ መካከል ያለ ደብዛዛ መልክ የሰካራም የሚመስል ሸካራ ገጽታ ታድያ አንድ ቀን የመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት ፈተና ሰሞን ከተለመደው ቦታ ሳታገኘው ቀረች ወደ ግራም ወደ ቀኝም የጐሪጥ ማየቷን ትታ በሙሉ ዓይኗ ፈለገችው የለም ወደማትቀርበት ቤቷ ስታዘግም ቅር እያላት ነበር ለምን እንዲያ እንደተሰማት ግን ለራሷም ገርሟታል። ለምን። ጠዋትኮ በስልክ ዛሬ ባስር ሰዓት የመጨረሻ ስትል እርሷን እንደሆነ ገብቶኛልፊ አንተ ለምን አትረሳትም አለው እኔኮ ምን እንዳስነካችኝ አላውቅም ሰው አንድ ቀን ይታለሳል ሦስቴና አራቴ መታለል አለ። እሺ እኔ ልሂድ ቆይ እንጂ ትንሽ እንጫወት አለው ሀብቴ ይመሽብኛል አለና ሳይጨብጣቸው ወጣ አፌ ጫር ሯ ሰሶሞገ ሹምዩ ሀብቴና እንዳለ ዳርም የለሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዩዋት እኩል ነው በአራት ኪሉ ቀልጣፎች ሳይ በለመደው ድፍረት ከእንዳለ ቀድሞ ለከፋት ለራሱ ገንኖ ለሚታየው መልክና ቁመናው ደንታ ሰላልሰጠችም በጋዜጠኝነቱ ሊማርካትበድርቅናው ሊያምበረክካት ራሱን ክቦ ቀረባት እርሏ ግን ቅንጣት ትኩረት አልሰጠችውም እንዲያውም አጣጥላው ሄደች ያ እንኳን አንዳንዴ ደረቆቹ የአራት ኪሉ ጨላጦችልብ ለመስቀልና ለማጓጓት የሚጠቀሙበት አለበለዚያም ምንም የማያውቁት የቤት ውስጥ ድመቶችየሚያሳዩት የዓይን አፋርነት ምልክት ነው ለጊዜው በሴት ጉዳይ ዓይን ለበላ ድፍረቱ ቁብ አልሰጠውም ከዚያ ያለፈም ሊያስባት አልፈለገምየኋላ ኋላ ግን ሁለቱ ቶተቀራርበው በፍቅር ነደውና ጦፈው ሲያይ አዲስ ስሜት ቁጭትና ቅናትን ያዘለ ዕኩይ ህሳብ በህሊናው አቆጠቆጠ ለምን። የዳርምየለሽን ቀጥተኛ መጥፎነት ሳይሆን ቀላል የሚመስሉ ነገር ግን ለጥርጣሬ በር የሚከፍቱ አሉ እና አየሁን ተመርኩዞ ብዙ እዚህ ቦታዎችን እና እንዲህ አረገችን ሲያቀብለውእንዳለም ሰምቶ ችላ ሲልበትና የርሷን ጥሩ እያነሳ በር በሩን ሲዘጋበት በካንገት በላይ ግንኙነታቸው እንደቆዩ ህብቴ ሳቢ ጋይድን መቅረብ ይጀምራል ሳቢ ጋይድና ዳርምየለሽ የአንድ ሠፈር ልጆች እንዲያውም የልጅነት አብሮ አደጐች መሆናቸውን ሲረዳ ቀድሞውንም ወንዳወንድነቷን በርቀት ይወድላት ከነበረው ሳቢ ጋይድ ጋር ያለውን አግባብ በጥብቅ ያዘና ርግብን በጭልፊት ብሎ ተነሳየፍቅር ደላላእያሉ የአራት ኪሎና አካባቢዋ ወጣቶች ሲያዳንቋት የስማላት ሳቢ ጋይድ ገንኖ በሚነገርላት ተአምሯ ዳርምየለሽን ከእጁ እንደምታስገባለት እርግጠኛ ነበርሀብቴ ከዳርምየለሸ ፍቅርም ሆነ ጥላቻ እንደሌለው ራሱን ለማሳመን ቢሞክርም ሰለርሷ በተለይ ከእንዳለ ጋር ባላት ግንኙነት መጥፎ መጥፎዋን ከማሰብና ከመመኘት ሊመለስ አልቻለም በህይወቱ ከሚያውቃቸው ምሰለ ሄዋኖች ሁሉ በማንኛውም ነገር ዝቅተኛና ርካሽ አድርጐ ሊመለከታት ሊንቃትና ሊረሳት ይፈልጋል ነገር ግን አንድ ቀን ተከትሎ እንደለከፋትበልቡ እንደሚመኘው እርሱ ሳይሆን እርሷ እንደናቀችው ይባስ ብላም አብሮት የነበረውና በዕለቱ ምንም የመቅረብ ምልክት ያላሳያት እንዳለን ማፍቀሯ የፍቅር ቀልቧ አርፎበት ወይንም ደግሞ ከእርሱ የሚበልጥ መልክና ቁመና ወይንም ሊላ ውበት አይታበት ሳይሆን ሆነ ብላ እርሱን ለማብሸቅ የፈፀመችው ተንኮል ነው ብሎ ደመደመ በመሆኑም አንድ ቀን በሆነ ዘዴ ከእጁ ወድቃ እርሱም በተራው ንቆና ስቆ ሊተዋት ሏሊበቀላት ተነሳ በሌላ በኩል ደግሞ ሁልጊዜ ራሱን ከፍ አድርጐ የሚመለከትና በሌ ሎች መበለጡን አሜን ብሎ መቀበልን የማይወደው ምቀኛ ተፈጥሮው በዳርምየለሽ ዓይን ዝቅ ተደርጐ መታየቱን እየነገረው ራሱን ከእንዳለ ጋር በማነፃፀር ካላሰበው ፉክክርና ውድድር ውስጥ እንዲገባ አደረገው ሀብቴ ከአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ በውጭ ቋንቋና ሥነሑፍ የባችለር ዲግሪውን የተቀበለ ከመሆኑም በላይ ከእንዳለ በሁለት ዓመት ቀደም ያለ የሥራ ልምድ ሰላለው የዩኒቨርሲቲን ደጃፍ ያልረገጠውና ከኋላው የተቀጠረው እንዳለ በተሰለፉበት የጋዜጠኝነት ሙያ ከእርሱ ማነስ እንዳለባት ያምናል ይሀ እምነቱ እንዳለ ገና ሳይቀጠር ጀምሮ እና ከተቀጠረም በኋላ በንባብና በተፈጥሮ ማሰተዋሉ ያዳበረውን ዕውቀትና ተስጥኦ ተጠቅሞ ያሳየውን የሥራ ሰኬት የተመለከቱ አለቆቹ የሚሰጡት ከበሬታና ከጅምሩ ያሳደሩበት እምነት እንዳይዋጥለት አድርጎታል። አንቺ ብትደብቂውም ግንባርሽ ሁኔታሽ ይናገራልፁ ስትላት ከአፏ እንዳመለጣት ገባትና እንደገና ደንገጥ አለች ይልቅ ችግርሽን ብታካፍይኝ በምችለው ሁሉ ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ ለችግርሽ መፍትሔ የማላገኝልሽ አድርገሽ ብትገምችኝ እንኳን የሚስጥርሽ ጠባቂ የሃሳብሸሽ ተጋሪ ጥብቅ ጓደኛሽ መሆኔን አትርቪ ካላራቅቪኝ በቀር የእኔ ላንቺ ተፈላጊነትም ይበልጡኑ በዚህ በዚህ ጊዜ ይመስለኛልዬ እውነተኛ ጻደኝነት የህይወት ልውውጦሽ ነው አንደኛው የሌላውን ችግርም ሆነ ደስታ የሚጋራበት አለበለዚያማ ለየብቻቸው ከልለው የራሴ የሚሉት ችግር ካለ ሁለቱ አንድ በመሆን ፋንታ የተራራቁና በተወሰነ ጥቅምና ፍላጐት ዛበቻ ተገድደው የተቆራኙ ናቸው እኔና አንቺ ግን በእስካሁኑ እምነቴ ለየራሳችን ፍቅርና ህሊናዊ ደስታ ከልብ ተጎዳኝተናል ህይወቴ ህይወትሸ ህይወትሽ ህይወቴ ሆኗል ብዬ አምን ነበር አሁንም ቢሆን የእኔም እምነት እንዳንቺ ነው ሩቂ አለች ዳርምየለሽ ካደኛዋ እንደተቀየመቻት ተሰምቷት እይመስለኝምዴሪ ቢሆንማ ኖሮ እንኳንስ እንዲህ ወትውቼሽ ራስሽ ብቁም ነገር ፈልገሸ ትነግሪኝ ነበር ያሳለፍሻቸው ቀናትኮ ቀላል አይደሉም አሥራ አምስት ቀን ሙሉ ብቻሽን ስታለቅሽና ስትተክዢ የቆየሽበትን ጉዳይ ባልፈታልሽ እንኳ አብሬ እንዳለቅስልሽ የጓደኝነት ውይይቴን ትፈልጊ ነበር አንቺ ግን እንደ ሩቅ ሰው ከልብሽ ሳታገልይኝ አትቀሪም ዳርምየለሽ ጨነቃት የብቸኝነት መረብ ተብትቧትና በጭንቀት ተወጥራ በመሰንበቷ ከማንም በላይ የምትወደው ፍቅረኛዋን መገናኘት እንዳቃታት ሁሉ ሩቂያም ዛሬ ተቀይማት ከሄደች ዳግመኛ ራሷ ፈልጋ ልታገኛት ለመቻሏ ውጪ የመውጣት ድፍረቷን ተጠራጠረች እንዲያውም ህሊናዋን ሲበጠ ብጣት የሰነበተውና አምቃ ልትፈነዳየደረሰችበትን ሚስጥር የሩቂያን ቅሬታና ውትወታ ምክንያት አድርጐ ስሜቷ እንድትተነፍስ አስገደዳት ከልጅነቴ ጀምሮ በጭንቅላቴ ውስጥ የጥያቄ ምልክት ሠርቶ የኖረ ጉዳይ ነው እኔ ግን መልሱን ቀርቶ ጥያቄውን ለማሰብ ድፍረት አጥቼ ስሸሸው ኽረ እንዲያውም ስፈራው ያደግኩትፅ አንድም ቀን ካፌ ወጥቶ ከሰው ጋር ተነጋግሬበት ጠይቄም ኣላውቅም እስከ እስትንፋሴ መጨረሻም ላነሳው አልፈልግም ነበር አዳፍሜኻው የኖርኩት ከልቤ ልብ ውስጥ የተቀበረ ጥርጣሬ ልለው የማልችል ቅሬታ ነበር እንዲሁ ብቻ ከአባቴ በተለይም ከዘመዶቹ ጋር በነበረኝ ግንኙነትየመዝናናት ስሜት አይሰማኝም በእናቴ ላይ የምቀብጠውንእና የምመካውን ያህል በአባቴ ላይ ቁጥብሆ ነው ያደግኩት ለምን። ጻ እንዴ ለምን። ታዲያ ለምን ትፈልጊያቸዋለሽ። ምክንያት እየፈጠርኩኝ አራት ቀን ቀረሁ ለምን። እንዴ። ምንም የምታውቀው ነገር የለም አለና ወደ ራሱ ጠረጴዛ ሄደ እሱን እንኳን ተወው። ሁል ጊዜም ያሳዝናታል ገመና ዳሺ ዳርምየለሸ ብቻዋን ተሸክማ ስትጨነቅበት እና ስታብጠለጥለው ሳይታወቃት ራሷን ለአካላዊና መንፈሳዊ ጉስቁልና የዳረገችበትን ችግር እንደሲኦል ከብዶና ቀፍፎ ያስፈራትን አባት የለሽ ህይወት በማወቅና ባስማወቅ በማመንና ባለማመን መሃል እያመነታች በውስጧ ሲፋጭና ሲተራመስ የሰነበተውን የህሊና ቁስል ለጓደኛዋ ካካፈለቻት ወዲህ መፍትሂውን ባታገኝለትም በመተንፈሷ ብቻ በመጠኑ ቀለል ብሏታል ሩቂያም ከቅዳሜ ዕለት ወዲህ እሁድና ሰኞን እየመጣች አጽናንታታለች ሆነ ብላም ሻይ ወይንም ቡና እንድታፈላላት ትጠይቃትና ለሥራ ጐንበስ ቀና ስትል ከሃሳቧ እንድትሸሸ ታደርጋታለች አንድ ሁለቴ ካየችው በኋላ ግን ራሷ ዳርምየለሸም የጉልበት ሥራ ጥሩ የሃሳብ ማቃለያ መሆኑን ተገንዝባ በቤት ሥራ እናቷን መርዳቱን ተያይዛዋለች አልቀነስ ያላትና መፍትሔ ያጣችለት ነገር ቢኖር የለሊቱ ሃሳብና ጭንቀት ብቻ ነው ዛሬም ከጧት ጀምሮ በልብስ አጠባ ነው የዋለችው ወይዘሮ ብዙ በነዚህ ሦስት ቀናት ልጃቸው ያሳየችው ለውጥ እያስደነቃቸው ነው አንዴ ፈጣሪያቸውን ሌላ ጊዜ አባ ደርብን እያመሰገኑ ለቅድስት ማርያም የተሳሉትን ያስር ብር መጋረጃ በሚቀጥለው ክብሯ ዕለት እንደሚያስገቡላት ደጋግመው ቃላቸውን ያድሱላታል እማማ ሸዋም አሥር አሥር ጊዜ እየመጡ በምክራቸው ውጤታማነት ተደስተው እሳቸውኮ ለሁሉ እሺ አይሉም እንጂ መዳኒት ናቸው ይላሉአባ ደርብን እያሞካሹ ቀለብተኞቹም ለምሳ ሲመጡ ዳርም የለሽን ከደጅ ሲያይዋት ተደስተዋል ሩቂያም ገና የአጥሩን በር ስትገባ ዳርምየለሽ ፈገግ ስትል በማየቷ አብዴት ፈገግ አለች ቆ ፆ ፋቆ አባባ ከፍ ያለው ናቸው ጠላቴ አለች የቆረስችውን እንጀራ ወጥ ሳታስነካ እጂ ላይ እንዳለ በጥርሷ ነክሳ አጠባውን ጨርሳ በወሮ ብዙነሸ መኝታ ቤት ምሳ እየበሉ ነው እንዴት። እናትክንና አንተ እኔኮ ምንም ይሁን ምንም ወንድ አሸንፎኝ አያውቅም አለችው ታዲያ የመውደድ ከሆነ ለምን ያን ያህል ተፋለምሽኝ። አለ ለምን። በርግጥ አባ ደርብ እንዳሉ ተለክፋ ቢሆን ለልጃቸው መድሃኒት የተባለ እንኳን ገንዘባቸውን ነፍሳቸውን ከፍለው ቢያድኗት ፈቃደኛ ናቸው ዛሬ ለአባ ደርብ የሚሰጡት ገንዘብ ግን መበለጥ መሆኑ ተሰማቸው ወደ እርሳቸው የሄዱበትን ቀን ረገሙ ቡናው ሲያከትም ወጥተው ለመሄድ ወሰስኑ ቀለብተኞቻቸው እሁድ እሁድ ስለማይመጡ ሥራ የለባቸውም ሲያሳስባቸው የቆየው የልጃቸው ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየተሻሻለ መምጣቱ ተመስገን ያሰኛቸውን ያህል ጭንቀቷ ወደ እርሳቸው ተጋብቶ ሰሱሞገ ሹምዩ ኤሥ ዴዴ ቆሎ ምጫ ሙጫ ቦም ሥ ሥሙ ምሥጢ ምሥኢ ራ ሲተክዙ ነው የሰነበቱት እውነትና ንጋት ሆነና ምንም ያህል ቢጠ ነቀቁና ሚስጥራቸውን የጠበቁ መስሎ ቢስማቸው ሲፈሩትና ሲሸሹት የኖሩት ጥያቄ አልቀረላቸውም ምንም ያህል ተንከባክበው ቢያሳድጓት ምንም ያህል ልጅነቷን ከአቶ ባህሩ አባትነት ጋር አያይዘው ውሸት ሲለመድ እውነት ይሆናል እንዲሉ ያህል ራሳቸውን ሳይቀር አሳምነው ለዚህ ቢያደርሷት እርሳቸው ባላወቁት ምክንያትና ባልጠበቁት ጊዜ ሚስጥራቸውን ሰምታ የማን ልጅነቷን እንዲነግሯት አፋጥጣቸዋለች የማን ልጅ ይበሏት። ልጅቷ ደግሞ ከሁኔታዋ ገና ምንም የማታውቅ የቤት ልጅ ትመስላለች አለ እንዳለ እሱ እንኳን የወጣላት የተቃጠለች ጭስ ናት። ካንጀት ካለቀሱ እንባ አይገድም ከዛ በፊት እንኳን ያን ያህል ቀን ሁለት ቀን ሦስት ቀን ለሥራ ወጥተህ ስትመለስ መንገድ ላይ ሳይቀር ሰመኸኝ አታውቅም። ምነው በቀደም ተነጋግረን የለም እንዴ። የምን አንድ ቀን። አለ እንዳለ ትንሽ ደንገጥ ብሎ በመገረም መርማሪ ፖሊለ ነኝ በመቶ አለቃ ማዕረግ ዛሬ እረፍት ስለሆንኩ ነው የደንብ ልብሴን ያልለበስኩት ይኸውልህ ሥራ የፈታ ፖሊስ ቁማር ይጫወታል አለና በራሱ ንግግር ከት ብሎ ሳቀ እኛስ መች አረፍን አለ እንዳለ አብሮት እየሳቀ እንዲህ ነዋ። አለ መቶ አለቃው እረ ካመጡትስ አንድ መልስዎ ያጣሁለት ጥያቄ አለኝ ይኺ ሲል እንዳለ መቶ አለቃ ጣልቃ ገብቶ አቋረጠው አቶ እንዳለ አንቱ እምባል ነኝ እንዴ። ይኹ ምንድነው። ገመና እንዴ። አለች ዳርምየለሽ የተከፋ ፊቷን ቀና አድርጋ ምን ለማለት እንደፈለጉ ገብቷታል እርሷም ሌላ አማራጭ እንደሌላት ታውቀዋለች እንጂ እኔ ብዙነሽ ተከብሬ በኖርኩበት ሠፈር ልጂ ዲቃላ ወለደች እየተባልኩ የለቅሶ ቤት አፍ መክፈቻ የቡና ላይ መተረቻ መሆን አልፈልግም እዚችው ተደብቀሽ ትወልጃለሽ ከዚያ በኋላ የማይታወቅ አገር ጉዲፈቻም ቢሆን እንሰጣለን አሉ እንደ አዲስ እየተናደዱ ስለዚህ ጉዳይ ለማንም ትንፍሽ እንዳይሉ ለልጆቻቸው በሙሉ ልመናም ማስጠንቀቂያም አዘል መመሪያ ሰጡ ከዚያ ቀን በኋላ ከውጪ በሚመጣም ሆነ በሚጠይቅ ሰው ሁሉ ስለዳርምየለሽ የሚታወቅ ነገር ቢኖር ከአዲስ አበባ ውጪ ስለመሄዲ ነው ደብረ ብርሃን አንድ የኔ ዘመድ አለ እዚህ ከምትቀመጥ ሥራ አስይዛታለሁ ብሉ ወሰዳት ይላሉ ወይዘሮ ብዙ ዳርምየለሽ የት እንደሄደች ለሚጠይቃቸው ሁሉ በተረፈ ከቤተሰቡ አባላት በስተቀር ወደ መኝታ ቤት የማንም ሰው እግር ቀርቶ ዓይን ዝር እንዳይል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ ከውጪ ሰው የሚገባ ቢኖር ለዚያውም ስትገባ ወይንም ስትወጣ ሰው እንዳያያት ጥብቅ ጥንቃቄ እየተደረገ ሩቂያ ብቻ ናት እርሷንም ወይዘሮ ብዙ እንድትገባ አልወደዱም ነበር ዳርምየለሽ እንደተደበቀች አንድ ቀን መልሰዋታል። አነጋገሬ አላስደሰተህም መሰለኝ አለ ዶክተር ጭንቅላቱን ነቅንቆ ባንተ አይደለም ዶክተር እንዲሁ በራሴው ጉዳይ ነው ይቅርታ ግን አንተንም ረበሽኩሆ አለ ዶክተርን ቅር እንዳይለው ያለልቡ ፈገግ እያለ ሳ ፌ ሪያን ምንም አይደል ይልቅ ጉዳዩን ለማወቅ ሩቅ ካልሆንኩኝ በቀር ብትነግረኝና ችግርም ከሆነ ቢያንስ በሃሳብ አለዚያም ጆሮዬን ሰጥቼ እንኳን እህ ብልህ ቀላል አይደለም። ይቅርታ እንዳለ። ኖኖ ምንም አይደለም እንዳለ። አለች ታዲያ የት ነው። እሱ ልክ ነሽ ለምን እንዳላፍብኩት እንጂ ይቻል ነበር አለ በሰበብ እማይገፋ ጥያቄ ሆኖበት እኔ ደግሞ ጋዜጠኞችን እንደሚጽፉትና እንደሚያወሩት ቁም ነገረኞች አድርጌ ነበር የማያቸው እኔኮ ሁሉን አልወክልም ስንት ቁም ነገረኞች አሉ መሰለሽ ዛሬ አሥራ ስድስት አይደል ከገባን ብላ ስንት ቀን እንደሆናቸው ለማሰብ ዝም አለች ነሐሴ ዘጠኝ ነው የገባነው ልክ ሳምንታችን አለና እንዳለ ቀደማት ሳምንት ብቻ ብዙ ቀን የሆነን ነው የመሰለኝ የክረምት ቀናት አይገፉም እባክህ። አለና አድናቆቱን ለሃብቴ ሲገልጽ አንድ ነገር እንደዋዛ ካጫወትከው ቃል በቃል አይረሳትም የማስታወስ ችሎታው ከፍተኛ ነው ማለት ነው አለ ሀብቴ አፉን ከለል እያደረገ ከማስታወሱም ለኢትዮጵያዊ ባህሳችን ያለው ጉጉትና ስሜት በጣም ነው የሚገርመኝ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ምን ያህል እንደሚያጓጓና የሀገር ፍቅር ስሜቱ ምን ያህል እንደሚያቃጥል ከሀገሩ ርቆ ባህር የተሻገረ ነው የሚያውቀው አየሀ እኔ በፊት ያን ያህል ነበርኩ ፈረንሳይ ሆ ግን በጣም ይሰማኝ ነበርሱ ሌላው ስለአገርህ በታሪክ የሰማውን ከመጻህፍት ያነበበውን ይዞ ለማረጋገጥ ሲጠ ይቅህ አላውቅም ማለቱ እንዴት ያሳፍራል መለለህ አገሬን አላውቅም ማለቱ እራሴን አላውቅም የማለት ያህል ነው ካገር ሲርቁ ሁሉ ነገር ይናፍቃል ሁሉ ነገርም አምሮ ይታይሃል እዚህ ሆነን የምናንቋሸሸውና የምናጥላላው ነገር ሁሉ ራቅ ስንል ተወዳጅ ሆኖ ትዝ ይላል አገሬን እንደምወዳት ያወቅኩት እዛ ሆኝ ነው አለ ዶክተር እኔ እንዲያው ያሳደርከብኝን አድናቆት ለመግለጽ ያህል ነው አለ እንዳለ ጥቂት ዝምታ ሰፈነና እንዳለ ገለጻውን ቀጠለ ሁሉን በዝርዝር ሳይሆን ያው እንደለሞኑ የማስታውሰውንና ለየት ያሉትን ነው የምነግርሀ ሰሱሞገ ሹምዩ ሴቢያን ይሁን አለ ዶክተር በጉጉት ጆሮውን ሰጥቶት። አለና ዶክተርን መጣሁ በሚል አተያይና ሁኔታ ትቶት እንዳለ በሄደበት አቅጣጫ ተከተለው ዶክተር እሺታውን ባንገቱ ይግለጽለት እንጂ በዛው ቢቀርም ደንታ አልነበረው ለምን እንደሆን ለራሱም ባይገባው ሃብቴን ና ሲያየው አልወደደውም የበደለውም ሆነ ያደረሰበት ጉዳት የለም ስላለፈ ህይወቱም ሆነ ስላለበት የሚያውቀው ክፉና በጐ የለም ትውውቃቸው ከዛሬ ጋር አራት የመጠጥ ቀናት በዚያው ቡና ቤት ነው እንዲሁ ብቻ ያስጠላዋል ረቡዕ ማታ እንዳለ ሲያስተዋውቃቸው አላማረውም ነበርሱ የተልፈሰፈሰ አጨባበጡ እሽኩርምም አስተያየትና አነጋገሩ ተባዕታዊ ተፈጥሮና አቋሙን የሚቃረን ነው ልምምጥ ከሚመስለው ትህትናው ጀርባም የተደበቀ ተንኮልና ሚስጥር ሳይኖር እንደማይቀር ጠርጥሯል ሁን እንጂ ጥርጣሬውም ሆነ ጥሳቻው በይፋ እንዳይታወቅበት ተጠ ንቅቋል ከእንዳለ ጋር አንድ ቢሮ እስከሠሩ ጥብቅ ጓደኝነት ቢቀር ቅርርቦሽ እንደማያጡ ገምቶ ሁለቱንም በአንድ ዓይን ለማየት ሞክሯል ልቡ ገን ለዘላቂ ጓደኝነት ላጨው እንዳለ አድልቶ ኮከቡ ያልገጠመለትን ሀብቴ ማግለሉ አልቀረም ከሁሉም ከሁሉም ዝምታ ማብዛቱን አልወደደለትም እንዳለ ግን ጥሩ ጓደኛ ሊሆነው እንደሚችል የተረዳው ገና የተገናኙ ሰሞን ነው ከመጠጥ ባሻገር ሁለገብ ጓደኝነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ቢመኝም ጊዜና ሁኔታ አላመቸውም ፋፊ ቆ ቱ ሸኖ ወርደናል። ምንም አለና ቅልስልስ ኮስተርተር በሚል ድብልቅ ስሜት ቀጠለ ካንተ እምፈልገውና አንተን የሚጐዳ ምንም ነገር የለም ልዘርፍህ ወይንም ልገድልህ አይደለም ያስገደድኩህ እንዲያውም ማስገደድ አይባልም ታዲያ ምንድነው እሚባለው ሳላስብና ሳልጠብቅ በጓደኝነት ስም ሰንጢ መወደርህ ፍቅር መሆኑ ነው። አለ እንዳለ ግራ ገብቶት ያው ከበደ ነዋ። በርግጥም ለእርሱ ትንሽ ናት እርሱ የመጀመሪያ እርሷ የመጨረሻ ልጅ በመሆናቸው በመህላቸው ራቅ ራቅ ብለው የተወለዱት ሶስት ወንድሞቻቸው የፈጠሩትን ልዩነት ያህል ይበላለጣሉ ለዚህም ነው ዶክተር በትምህርት ችሎታዋ ዐዋቂ አድርጉ የሚያያትን ያህል በታላቅነት አቀራረቡ ደግሞ እንደ ትንሽ ልጅ የሚመለከታት ማንም ሰው እኛ ከምናውቀው ሌላ የየራሱ ድብቅ ሰብዕናና ህይወት አለው ለዚህም ነው ስለሰው ልጅ ባህሪይና አፈጣጠር ማጥናት በዓለም ላይ ካሉት ላይንሶች ሁሉ እጅግ ከባድና አስቸጋሪ ነው የሚባለው ጓደኛሽ ከዚህ ውጪ ልትሆን አትችልም የምታውቂውን ያህል ተናገርሽ እንጂ ጓደኛሽ ሌላ ህይወት ሌላ ሚስጥር ሊኖራት አይችልም ብለሽ መሟገት አትችይም አለና ለምን እንደተለያዩ ማወቅ የሚችሉት ሁለቱ ተፋቃሪዎች ራሳቸው መሆናቸውንና ምክንያት ብለው ለየራሳቸው የሚያወሩት አውነት ሊሆንም ላይሆንም እንደሚችል አስረዳት ሩቂያም እንዳሰ በዳርምየለሽ ላድ ካደረሰው በደል አንፃር ይቅርታ የማይገባው ጥፋተኛ መሆኑን ብታምንጂ ለምን እንደዛ እንዳደረገ ግን በርግጥም ዳርምየለሽ ከነገረቻት በስተቀር የእርሱን ምክንያት አለማወቋ የወንድሟን ሃሳብ እንድትቀበል ኣስገደዳት ይክተር አብደላ እህቱን ካረጋጋ በኋላ ወደውጭ እንደማትሄድ አረጋገጠና ወደ እንዳለ ተመለሰ አጠቃላይ የታሪኩን ሚስጥር ለማወቅ ጓጉቷል ስሱሞገ ሹምዩ ይቅርታ እንዳለ ብቻህን አስቀመጥኩህ ለተፈጠረው ችግር በጣም አዝናለሁ ምንም አይደል ዶክተር። አስወርዳ መተኛቷን ከማን እንዳስወረደች ሳይቀር የሠ ፈሯ ከሆነች ልጅ ሰማሁ አለ ያን ጊዜ ማሰወረዲን ሰምቶ እንደገና ማመኑና መታለሉ እንዳዲስ እያናደደው ዶክተር እንዳለ በጠቀሰው ጊዜ ዳርምየስሸ መታመሟን እንጂ ማስወረዷን ከሩቂያ ስላልሰማ አስቀድሞ እንደገመተው በሁለቱ መሃል ብቻ የቀረ ምስጢር ስለመኖሩ ርግጠኛነት ተሰማው ቢሆንም አጣርቶ ለመረዳት የእንዳለን ምክንያት በቀጥታ አልተቀበለውም ይቅርታ አድርግልኝና የሰሙት ሁሉኮ እውነት አይደለም ሰማሁ ብሎ ፍቅርን ያህል ትልቅ ነገር ማፍረስ ተገቢ አይደለም ፍቅር በተዘጋ ቤት ውስጥ እንደሚያነዱት ሻማ ነው በርና መስኮት ሲከፈት ሻማው ለንፋስ እንደሚጋለጥ ሁሉ ዓይንና ጆሮ ሲከፈት ደግሞ ፍቅር ስወሬኞች ይጋለጣል ታምናት እንደነበር ነግረኸኛል በትክክል ካፈቀርካት አለስመገናኘታችሁንና ከለው የሰማኸውን አሉባልታ ምክንያት አድርገህ እምነትህን ማፍረስ አልነበረብህም ለእምነት ከማመን በቀር ምንም ማረጋገጫ መንገድ የለውም በእምነትህ ላይ ጥያቄ አንስተህ መልሱን ከሌሎች ከጠበክ ጥርጣሬ ላይ ነህ ጥርጣሬ ደግሞ ጠንካራ ካልሆነ እምነት የሚያቆጠቁጥ የህሲና ረብሻ ነው እኔ አንተን ብሆን ብሎ ዶክተር በወቅቱ ይወስድ የነበረውን ርምጃ ሊናገር ሲል እንዳለ አቋረጠው ዶክተር ያልገባህ ነገር አስ እኔ ይኹንን ብቻ መነሻቫ አድርጌ አልተጣላኋትም በርግጥ ለጊዜው ተስፋ ቆርጩ ለመተው ወስጌ ነበር። አለና ጠየቀው አንድ ጊዜ ብቻ። አለ እንዳለ ሲገልጽለት ውሎ የዶክተር እንደ አዲስ መጠየቅ አስገርሞት ማርገዚን ነዋ አኔ ተጠንቅቄና ጊዜያዊ ስሜቴን ተቆጣጥሬ አስተማማኝ በሆነ ቀን እስከወጣን ያረገዘችው ከኔ ነው ብዬ ላምንም ሆነ ልቀበላት አልችልም ከእኔ ጋር ያላት ግንኙነት በዚህ የመከላከያ መንገድ እስከሆነ ደግሞ ከሌላ ለማርገቧ ምንም የሚያጠራጥር ነገር የለም ክሌላ ማርገዚ ደግም ከኔ ሌላ ሰው ታውቅ እንደነበር በፊት ሰምቼ ለናቅኩት ወሬ ሁሉ ማረጋገጫ ነው ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ አለ። አለው ምንም አይደል አለና ከፊቱ በክቡ ጠረጴዛ ላይ ካሉት የፈረንሳይኛና እንግሊዝኛ መጽሔቶች አንዱን የእንግሊዝኛ አነሳ የተረጋጋ ለመምሰል እንጂ ስዕል ስዕሉን እየመረጠ እንደሚያይ መሃይም ገጾቹን ቶሎ ቶሎ ከመግለጥ በቀር አንድም የሚያስተውለው ነገር አልነበረም ልቦናው እዚያው ግራ መጋባቱ ላይ ነው ዶክተር አብደላ ፒ ኤች ዲውን ያገኘው በተለይ በልብ ህክምና ቢሆንም በሌሎች የህክምና ዘርፎችም ላይ ያለው ዕውቀት በቀላሉ የሚገመት አይደለም በተለይ ፈረንሳይ አገር በቆየባቸው የትምህርት ዓመታት ከራሱ የጥናት ዘርፍ ውጪ ሌሎችንም ባለው ጊዜና አቅም ሁሉ ከሳይብረሪ ከመምህራንና ከሌሎችም የዕውቀት ምንጮች ደህና አድርጉ ቀስሟል አዲስ አበባ ከተመለለም ከፖሪሰ ይዚቸው ከመጣቸው ጋር በየአንዳንዱ የህክምና ዘርፍ ላይ ያተኮሩ በርካታ መጻህፍትን ገዝቶ መደርደሪያውን ሞልቷል እናም ከሥራና ከማህበራዊ ኑሮ የተረፈውን ጊዜ የሚያሳልፈው ከነዚሁ መጻህፍቱ ጋር ነው ከሙያ ባልደረቦቹም ሆነ ከአንዳንድ ህሙማን ስለማንኛውም ዓይነት የጤና ችግር ከተወያየ ወይንም ራሱ ትዝ ካለው እቤት እንደገባ የሚመለከተውን መጽሐፍ ያገላብጣልከሁሉም በላይ ደግሞ የሥነአዕምሮ ህክምና ላይ ማተኮር ይወዳል በርካታ የሳይኮሎጂና የሳይኪያትሪ መፃሕፍትም አሉት ይኸው ዝንባሌና ትኩረቱ ሳይሆን አይቀርም ሁልጊዜም የሰዎችን ውስጣዊ ችግር ጠለቅ ብሎ እንዲያውቅና ካወቀም በኋላ ለመርዳት የሚገፋፋው አሁንም በጣም የሚወደው ምግብ ሲቀርብ አይቶ ለመብላት እንደቸኮለ ሰው በጉጉት ተወጥሯል ሁለቱ ፍቅረኞች የተጣሉበትን ሜስጥር ለራሱ ቢረዳውም እንዳለ መቶ በመቶ እውነት ብሎ ያኖረውን እምነት ከጭንቅላቱ በፍጥነት ጠራርጐ በማውጣት ትክክለኛውን ሁኔታ ባጭሩ ሊያሳምንለት የሚችለው አንዳንድ ነጥቦችን ከመጻህፍት እየመረጠ ቢያስነብበው መሆኑን አምኖበታል ያለዚያማ በንግግር ብቻ የእንዳለን ጥያቄዎች መመለሱ ከባድ ነው ከሦስቱም መጻህፍት በየማውጫቸው መሠረት የሚፈልጋቸው ነጥቦች ያሉባቸውን ገጾች ጠርዝ አጠፍ እያደረገ ምልክት ከያዘ በኋሳ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጣቸው ይቅርታ እንዳለ ለምጠይቅህ ጥያቄዎች ያለቅሬታ መልስ ስጠኝ። ጭሥ ኤ ሥሥጮጄሥ ኢፌም ኢፌም ዮኢ ሥሥ ኢኢ ሥሥ ሚራ ገመና አታውቅም ብዬ ሳይሆን ውይይታችንን ቀላል ስለሚያደርገው ነው እንዳለ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ እሺታውን ገለፀለት እስቲ በቅድሚያ ስለተፈጥሮ የወሊድ መከሳከያ ዘዴዎች የምታውቀውን ንገረኝ ማለቴ የሚረገዝባቸውና የማይረገዝባቸውን ቀናት ለይተህ አለና መልስ ከማግኘቱ በፊት ባዶ ወረቀት ከእስክሪፕቶ ጋር አቀረበለት እዚህ ላይ በግራፍ መልክ ብታስቀምጠው ይቀልሃል እንዳለ እስክሪገቶውን በእሺታ ቢቀበልም የሚነጋገረው ከሐኪም ጋር መሆኑን አሰበና በጉዳዩ ላይ ያለውን እውቀት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጠረ ይሁን እንጂ አንዴ ማወቁን ስለተናገረ የሚያውቀውን ማሳየት እንዳለበት ተለማው እናም እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከወረቀቱ ግራ ጠርዝ ወደ ቀኝ ቀጥታ መስመር አለመረ በመስመሩ መሃል ላይ አሥራ አራት ቁጥርን መጀመሪያው ጫፍ አንድ ቁጥርን በመጨረሻው ጫፍ ሃያ ስምንትን ጻፈ ቀጥሎም አምስትን አሥራ አንድን አሥራ ለባትን በየግምት ቦታቸው ላይ አሰፈረ ቀናት መሆናቸው ነው ከአንደኛው እስከ አምስተኛው ቀን ሜኑስትሬሽን ፔሬድ ነው አለ ዶክተርን በጥርጣሬ እያስተዋለው ዶክተር ግን ተቃውሞም ድጋፍም ሳያሳይ እንዲቀጥል ጠበቀው ባነበብኩት መሠረት የማስታውሰውን ያህል ነው አለና ቀጠለ እንዳለ ከመጀመሪያው ቀን እስከ አሥረኛው ቀን ነፃ ቀናት ሲሆኑ ከአሥራ አንደኛው እስከ አሥራ ሰባተኛው ቀን የሚረገዝባቸው ቀናት ናቸው ከአሥራ ስምንተኛው እስከሚቀጥለው የወር አበባ መምጫ ያሉት ቀናት ደግሞ ነፃና የማይረገዝባቸው እኛ ስንጠቀም የነበረውም መጥቶ ከሄደ በኋላ የእርሷ ሶስት ቀን ብቻ ነው የሚቆየውሃ በሚቀጥሉት ሰባት ቀናት እና ይመጣል ብለን ከምንጠብቅበት ሰባት ወይንም ስምንት ቀናት ውስጥ በሚኖረው እሑድ ነው ይኹ ደግሞ ከመጽሐፉም ይበልጥ አስተማማኝ ይመስለኛል እሺ። እንዳለ መጽሐፉ በሕክምና ቋንቋ የተጻፈ በመሆኑ ስለከበደው በሙሉ ሊያነበው አለመቻሉን እና በወር አበባ ዑደት የቀን አቆጣጠር ላይ የተመሠ ረተውንም የመቆጣጠሪያ ዘዴ የተረዳው በቻርት የተደገፈ ስለነበር መሆኑን ነገረው ዶክተር ሌሎችንም እንዳለ ስለተፈጥሮ የእርግዝና መከላከያ መንገዶች መመረ እውቀት የሚመዝኑ ጥያቄዎች ካነሳ በኋላ ነው የራሱን ማብራሪያ የጀመረው በቅድሚያ ክጠበ ዚሀርከበ ከሚል መጽሐፍ ላይ ሴቴ የመራቢያ ዘዴ በሚል ርዕስ ሥር ስለወር አበባ ዑደት ስለ የሴት ዕንቁላል መፈልፈል ፅንሰት እና የፅንስ እድገት የመጀመሪያ ደረጃዎች የሚያለረዳውን በስዕል የተደገፈ ጽሑፍ ለእንዳለ ይከብዱታል ብሎ ያሰባቸውን የባዮሎጂ ቃላት ከአናታቸው ተቀራራቢ የአማርኛ ፍቺያቸውን በእርሳስ ጽፎ እንዲያነብ ሰጠው በቅድሚያ ሲስተሙን እንድታውቀው ነው በማንኛዋም ሴት አካል ላይ ከኩላሊት በታች ከሆድ የኋለኛው ግድግዳ ግራና ቀኝ ተያይዘው የሚገኙና ኦቫሪየሚባሉ ሁለት የሴቴ እንቁላል መፈልፈያ እጢዎች መኖራቸውን እነርሱም አንዲት ሴት ልጅ ከመወለዷ በፊት ተፀንሳ እያለች ማደግ እንደሚጀምሩና ከተወለደች በኋላ አዲስ የሚፈጠር እንቁላል እንደሌለ በእንቁሳል እጢዎች አማካኝነት ይዛቸው ከምትፈጠረው በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠሩ በየራሳቸው የሚያድጉ እንቁላሎችም አብዛኞቹ ተፈረካክሰው ሲቀሩ የተረፉት ቀስ በቀስ እድገታቸውን እያሟሉ ልጅቷ ለጾታዊ ብስለት ወይንም ኩርድና ዕድሜ ስትደርስ ከአሥራ አንድ እስከ አሥራ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ እንቁላሎቹ ከሁለቱ መፈልፈያዎቻቸው በየተራ አንድ በአንድ እየሆኑ መውጣት እንደሚጀምሩ ይም አንድ በአንድ ከእንቁላል እጢዎች የሚለቀቁበት ሂደት ኦቭዩሌሽን ማለትም የእንቁላል መፈልፈል ሂደት እንደሚባል አንዲት ሴት ከኩርድና ጊዜ እስከ እርጣት ወይንም የእንቁላል መፈልፈል እስከሚቆምበት ሃምሳ ዓመት ዕድሜ ገደማ ድረስ አምስት መቶ ያህል እንቁላሎችን ወደ ማህፀኗ ኦቪደከት በተሰኘው የማህፀን ቧንቧ በኩል እንደምትለቅ የወር አበባ ዑደት የምንለውም በነዚህ ጊዜ አት የሚኖረውን መደበኛና ወርሃዊ የሴቴ መራቢያ ዘዴ ተደጋጋሚ ከንውን መሆኑን ይህ ተደጋጋሚ ክንውንም ከእንቁላል ዕጢዎች እና አንጐል ውስጥ ከሚገኝው ፒቱታሪ ግላንድ የተለኘ ዕጢ በሚመነጩ ሆርሞኖች የተወሰኑ የማነቃቂያ ኬሚካሎች ቁጥጥር የሚካሄድ ስለመሆኑ ወንዴው ዘር ሴቴውን እንቁላል አጥቅቶ ሲዋሃድ ፅንሰት ተካሄደ እንደሚባል ከዚያም ደረጃ በደረጃ ወደ ቀዳማይ ፅንስነት አድጐ ሙሉ ለሙሉ በማህፀን እስኪፀድቅ የሚኖረው የመዳበር ሂደት የመጀመሪያ ደረጃ የፅንስ እድገት እንደሚባል በስዕላዊ መግለጫውና በዶክተር ማብራሪያ እየታገዘ አነበበ ዶክተር አብደላ እንዳለ ለመረዳት የቸገረውን ሲጠይቀው ባጭሩ ከማብራራት በስተቀር ከእንዳለና ፍቅረኛው መለያየት አኳያ ያለውን ግንኙነት ላለማንሳት እየተጠነቀቀ ነው እንዳለም ለመጠየቅ አልቸኮለም ሲያነብ አልገባ ያሉትን ቃላትና ዐረፍተ ነገሮች ብቻ ነው የሚጠይቀው ቀጠለ ንባቡን በወር አበባ ዑደት ውሰጥ ከአሥራ ሦስት እስከ አሥራ አምስተኛው ቀን በማንኛውም ጊዜ የእንቁላል መፈልፈል ሊካሄድ እንደሚችልና የተፈለፈለው አንቁላልም ለሰላሳ ስድስት ሰዓታት ያሀል ለመጠቃት ዝንጁ ሆኖ እንደሚቆይ የወንዴው ዘርም ከተረጨ እስከ ሦስት ቀን በሴጃ ማህፀን ውስጥ ሳይሞት ወይንም ለማጥቃት ዝግጁ ሆኖ መቆየት እንደሚችል ከዚህ በመነሳትም ከአማካዩ የእንቁላል መፈልፈያ ማለትም አሥራ አራተኛው ቀን ሦስት ወደኋላ እና ሦስት ወደፊት በድምሩ ስድስት ተከታታይ ቀናት በፅንሰት ጊዜ እንደሚታቀፉ በዝርዝር አነበበ ስለወር አበባ ዑደት የሚያስረዳው ሠንጠረዥም ካሁን ቀደም ከሚያውቀው ጋር ተመላሳይ ነው የመፀነሻ ጊዚ ተብሎ የተቀመጠው ከአሥራ አንደኛው እሰከ አሥራ ሰባተኛው ቀን ያለው ሲሆን ከዚያ በፊትና በኋላ ያሉት ነፃ ቀናት ናቸው ምን አስቦ እንደሚያስነብበው ሊገባው ባይችልም በእርሳስ ምልክት አድርጐ የለጠውን ሁሉ አንብቦ መጨረሱን ገለፀለት ስዕሎቹንና ሠንጠረቱቹንም በደንብ አየሃቸው። ክ በ የሚለውን መጽሐፍ አንስቶ ፐከር ዚከነከጠ ርአክእከ ከሚለው ምዕራፍ በእሮሳስ ምልክት ያደረገባቸውን አንቀጾች እንዲያነብ ሰጠው የመጀመሪያው ርዕስ የእንቁላል መፈልፈያ ጊዜን ስለማስላት ነው የወር አበባ በትክክል መደበኛ ሆኖ የሚመጣ ከሆነ በአንደኛውና በተከታዩ ፔሬድ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት ወይንም ሦስት ቀናት ሊበልጥ እንደማይችል እና ይህንኑ መሠረት በማድረግም ከረዥም ጊዜ ክትትል በኋላ የወር አበባ ሂደት መግለጫ ማዘጋጀት እንደሚቻል የእንቁላል መፈልፈያ ጊዜም የሚቀጥለው የወር አበባ ይመጣል ተብሎ ከሚጠበቅበት አሥራ አራት ቀን ቀደም ተደርጐ እንደሚሰላ ይገልፃል የእርግዝናና የማይረገዝባቸውን ቀናትም ከመጀመሪያው መሐፍ ጋር በተመሳሳይ ቀናት ያስቀምጣል ሆኖም በዚያ ብቻ የሚያልቅ ሳይሆን ሌሎችንም ከወር አበባ ጋር የተያያዙ የእርግዝናና የማይረገዝባቸው ቀናት መለያ መንገዶች ይገልጻል የሰውነት ሙቀትን ለክሊኒክ አገልግሎት በሚውል ቴርሞሜትር በመለካትና ከማህፀን የሚወጣውን ንፍጥ መሰል ፈሳሽ መጠንና ባህሪ በመከታተል እንዲሁም በእንቁላል መፈልፈያ ወቅት ተደጋግመው የሚመጡ የህመም ስሜቶችን በማጤን ለምሳሌ በታችኛው የሆድ ክፍል ወይንም በሽንጥ አካባቢ እንደውጋትና ቁርጠት ያሉ ህመሞችን የጡት ህመምና ሴሎችንም በመከታተል እርግዝናን መከላከል እንደሚቻል በማብራሪያው ማጠቃለያ ገደማም ከላይ በተዘረዘሩት ከወር እበባ ዑደት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ለውጦችንና የጊዜ አቆጣጠር ዘዴን በአንድነት ተቆጣጥረው ከሚጠቀሙት ጤናማ ሴቶች መካከል በዓመት ከአሥራ አምስት እስከ ሃያ አምስት በመቶ የሚደርሱት እርግዝና እንደሚያጋጥማቸውና ለዚህም ምክንያት የሚሆነው የእንቁላል መፈልፈያ ጊዜአቸው ልዩነት ሲኖረውና ምናልባትም ይኸው ጊዜ ከስድስት ቀናት ሊበልጥ ስለሚችል መሆኑን ይገልጻል በመቀጠልም ዘዴውን ለመጠቀም የማያስችሉ ችግሮችን ያስረዳል በዚህም የእንቁላል መፈልፈል ወቅትን በትክክል ለመገመት የማያስችሉ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ እንደሚችሉና ከነዚህም ውስጥ ብዙ ሴቶች በየጊዜው ወይንም አልፎ አልፎ የሚመጣ የእንቁላል መፈልፈል እማይካሄድበት ዑደት ስለሚኖራቸው የሰውነት ሙቀታቸው ለውጥ ሳያሳይ ስለሚቀር እና የሚቀጥ ለው የወር አበባ መምጣት ከሚገባው ጊዜ ቀድሞ ወይንም ዘግይቶ ሲመጣ ስለሚችል እንደሆነ በወር አበባ ዑደት ውስጥ ዘግይቶ ሊከሰት የሚችለውን የእንቁላል መፈልፈል ከመደበኛው ይልቅ ለማወቅ አለመቻሉ ዘዴውን ውድቅ ሊያደርገው እንደሚችል በዚህም ምክንያት ያልተጠበቀ እርግዝና ሊከሰት እንደሚችል በመጀመሪያውና በመጨረሻው የርባታ ህይወት ጊዜም አንዳንድ ችግሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተለይ ወጣት ልጃገረዶችን በተመለከተ ከመጀመሪያው የወር አበባ በኋላ እስከ ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ ሳለ ጊዜ መደበኛና የተስተካከለ የወር አበባ ዑደት አለመኖር እንደሚያጋጥም መደበኛ ዑደት ቢመሠረትም እንኳን እንደ ሰከንደሪ አምኖሪያ ማለትም ድኅረ ወር አበባ መቅረት ያሉ ያልተለመዱ ሁኔታዎች በተለይ ከአሥራ ስምንት እስከ ሃያ ሁለት ዓመት ያሉ ልጃገረዶችን እንደሚያጋጥሟቸው ይገልፃል ገመና ሦስተኛው መጽሐፍ ደግሞ ለክ ለሯ ሃበ የሚል ሲሆን ዶክተር ምልክት አድርጐ የሰጠው የወር አበባ መዛባት ምክንያቶች የሚለውን ርዕስ ነው ስለ የወር አበባ መቅረት ወይንም አለመኖር የሚያብራራ ነው ከመጀመሪያው የወር አበባ በፊትና ከእርጣት በኋላ የሚኖረው የወር አበባ አለመኖርና መቋረጥ ጤናማ ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው ፕራይመሪ ወይም ቅድመ ወር አበባ መቅረት ከጅምሩ ምንም ዓይነት የወር አበባ ሳይኖር አምኖሪያ መምጣት ከሚገባው ጊዜ ሲተላሰፍ ወይንም ሲዘገይ ነው ይኽውም የመጀመሪያው የወር አበባ መምጣት ያለበት ከአሥር እስከ አሥራ ስድስት ዓመት ዕድሜ ሲሆን ከአሥራ ስድስት አመት በኋላ ሳይጀምር ከቆየ ቅድመ ወር አበባ መቅረት ይባላል ሰከንደሪ አምኖሪያ ወይም ድኅረ ወር አበባ መቅረት ደግሞ ከጤናማ የወር አበባ ጊዜ በኋላ የሚከሰት መዛባት ነው ይኸውም አንዲት ሴት በመደበኛ ሁኔታ የወር አበባዋ እየመጣ ሳለ በመሃሉ የሚከሰት መቋረጥ ወይንም የወር እበባ አለመኖር ነው ሰወር አበባ መቅረት ምክንያቶቹ በርካታ ናቸው ከነዚህም ርግዝና አንዱ ሲሆን ሁልጊዜም የወር አበባ ሲቋረጥ እግምት ውለጥ መግባት የሚገባው ነው ሌላው የሥኑልቦና ጭንቀት ሲሆን በተሰይ ማህበራዊም ሆነ ስሜታዊ ጭንቀት ውስጥ የሚገኙ ልጃገረዶች ላይ የወር አበባ መቅረት የተለመደ ነው ለምሳሌ ከወንድ ጓደኛ ጋር በተያያዘ የፍቅር ችግር ከትምህርት መፈናቀል ከቤተሰብ ያለመስማማት በአደጋ ምክንያት እናት ወይንም አባትን እና ሌሎችንም ማጣት የመሳሰሉ የቤት ውስጥ ችግሮችና ሌሎችም የአዕምሮ መረበሽን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ከዚህም ሌላ እንደ ልክርዐርእ ሃያሉ ከአዕምሮ ህመም ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ የምግብ ጥላቻና ፈጣን የክብደት መቀነስ ችግሮች የወር አበባ መቅረትን ያስከትላሉ በተጨማሪም ልዩ ልዩ የትኩሳትና የዕጢ በሽታዎች በደም ውለጥ የብረትን መጠን የሚቀንሱ እንደ ደም ማነስ ያሉ በሽታዎች ያልተስተካከለ አካላዊ እድገት በማህፀን በብልትና በክሮሞዞም ላይ ሲያጋጥም የወር አበባ መቅረት ሊከሰት ይችላል አንብቦ ሲጨርስ በተምታታ ለሜትና ግራ በተጋባ የህሊና መሳከር ተዋጠ ዶክተር አብደላም ያሰነበበው ጽሑፍ በእንዳለ ላይ ያመጣውን የስሜት ለውጥ ለመገመት ትክ ብሉ ተመሰከተው አሎር። አለ ዶክተር የተሰማውን ቅሬታ እርግፍ አድርጐ ከመቀመጫው እየተነሳ ቅድም እንዳልኩህ አነሳሴ ለኔ የታየኝን ህቅ ለኔ የተገለፀልኝን እውነት ላሳይህ እንጂ ታረቅ አትታረቅ ልልህ ወይንም ጥፋቱን ባንተ አድርጌ እርሷን ንጹህ ለማለት አይደለም በወቅቱ በእርሷ ላይ የደረሰውን ጉዳት እኔ እንደምልህ በቤተሰባዊ ችግር ሳቢያ የመጣ የአዕምሮ ጭንቀት ወይንም አንተ አለችኝ እንደምትለው ስሱሞንገ ሹምዩ አሥ ዴዴ ዮዮ ም ኢም ሚኢ ምጧ ሇሚ ም ሌላ በሸታ ታምማ አድርገን እንውለድ የማስወረዲን ጉዳይም ለጊዜው እናቆየው ይሁንና የህሊና ወይንም የአካል ጉስቁልና ደረሰባት ብለን እናስብ አለና ወደ እንዳለ አስተዋለ እንዳለ ቀኝ ክንዱን ጠረጴዛው ላይ አሳርፎ አዝጩን እንደደገፈ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ መቀበሉን አረጋገጠለት የአዕምሮ መረበሽና ሌሎች የውስጥ ህመሞች ደግሞ ለወር አበባ ዑደት መዛባት በዋነኛ ምክንያትነት ከተጠቀሱት መንስኤዎች መሐል እንደሆኑ ካነበብከው ጋር እናገናዝብ አለና አሁንም ንግግሩን ገታ አድርጐ አስተዋለው እንዳለ ኤሌክትሪክ እንደያዘው ሰው መላ ሰውነቱን ነዘረው መሃል ጭንቅሳቱ ሲቃጠል ይሰማዋል ዶክተር ሊለው የፈለገው አስቀድሞ ገባው ሆኖም የተባለው የአዕምሮ መረበሽም ሆነ በሽታ እንበል ብለው የተስማሙበት እንጂ በዳርምየለሽ ላይ በትክክል የደረስ እንዳልነበር ሲያስብ ቀዝቀዝ አለና ራሱን ተቆጣጥሮ ቃል ሳይተነፍስ እንዲቀጥል ጠበቀው በተዛባ የወር አበባ ዑደት ደግሞ ትክክለኛውን የእንቁላል መፈልፈያ ወቅት ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ለእርግዝና ያሰብከው ላይረገዝበት ሴፍ ፔሬድ ያልከው ደግሞ ሊረገዝበት ይችላል በቀጥታ ወደ ዳርምየለሽና አንተ አጋጣሚ ብንገባ በደረሰባት የአዕምሮ ጭንቀትና የሰውነት ጉዳት ሳቢያ ከዚያ ቀደም በጤንነቷ ጊዜ ትክክለኛ ቀኑን ጠብቆ ይካሄድ የነበረው ኦቭዩሌሽን ከወትሮው ቀድሞ ወይንም ዘግይቶ ሊከናወን ይችላል ለምሳሌ ከመጻህፍቱ ባነበብነው መሠረት ከአሥራ ሦስተኛው እስከ አሥራ አምስተኛው ቀን ባለው ጊዜ መሃል መካሄድ ሲገባው አስከ አሥራ ስምንተኛውና አሥራ ዘጠነኛው ቀን ቢዘገይ አሥራ ዘጠኝን ለምሳሌ አማካይ አርገን እንውሰድ ሦስት ወደፊትና ሦስት ወደ ኋላ ባሉት ቀናት ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት ቢደረግ የማርገዝ ዕድል ሊያጋጥማት ይችላል ይህም ከአሥራ ስድስተኛው እስከ ሃያ ሁለተኛው ቀን ያሉትን ያጠቃልላል። እንዲያውም ክረምት ሲመጣ ውበታቸው ይጨምራል ዶክተር አብደላ ክረምትና አበባ ለምን እንደማይዋደዱ ሁልጊዜም ይገርመዋል እንዳለ በበኩሉ በዛሬው ቀን ከዶክተር ጋር የተነጋገሩትንና ያሰነበበውን ሁሉ አንድ በአንድ በህሊናው ከልሶ ከእርሱ የበፊት እምነትና ዕውቀት ጋር አገናዘበው ባለማወቅ የሠራው ስህተት መኖሩም ገብቶታል ሆኖም ሙሉ ለሙሉ ጥፋቱን ለማመን አንድ ነገር ግልጽ ሊሆንለት እንደሚገባ አሰበ ዶክተር ለዚህ ሁሉ ችግር ዋነኛ መንስኤ አድርጐ ያሳመነው በዳርምየለሽ ላይ የደረሰ የመንፈስ ጭንቀት ወይንም ሌላ የወር አበባ መዛባት ችግርን ሊያስከትል የሚችል ህመም ዓይነትሱ በሰውነቷ ላይ የደረሰውን ለውጥ ቢያስተውልም በውርጃ ምክንያት የመጣ መሆኑን አምኖበት የቆየ ግምት ነው ዶክተር። ዶክተር አብደላ አስተውሎቱን ወደ እንዳለ መለሰ በዳርምየለሸ ላይ መጀመሪያ የደረሰው የቤተሰብ ችግር ምንድነው። አለ ዶክተር እጂን ይዞ ገመና እንዴ። በተለይ ኑንሽና አስናቀች ድስት በጣዱና ሰሃን ባለቀለቁ ቁጥር ያለፍላጐጉቷም ቢሆን እያስጨነቁ በላይ በላዩ የሚያጐርሷት ምግብ ሰውነቷ መለስ ብሎ በቶሎ እንድትጠነክር ረድቷታል ያልተጠገነና ያልጠነከረ ነገር ቢኖር የህሊናዋ ቁሰል ብቻ ነው አሁንም ስለአባቷ ታስባለች አሁንም ስለ እንዳለ ፍቅርና በደል ታስባለች ጥያቄ ፍቅር ጥላቻ በቀል ይቅርታ በዚያ ላይ የእናቷ በእርሷ ምክንያት በሸታ ላይ መውደቅ የቱን ይዛ የቱን ረስታ መኖር እንደምትችል ግራ እንዳጋባት ነው በተለይ ደግሞ ስሞኑን ሩቂያ እና ምቋንም የማያውቀው ወንድሟ ዶክተር አብደላ የእንዳለን ጉዳይ በማንሳት የሚወተውቷት ከመጠን በላይ ሲረብሻት ነው የሰነበተው ለሩቂያ ያላት የጓደኝነት ፍቅር ከእርሷም አልፎ ወንድሟ እናቷ ከታመሙ ጊዜ ወዲህ የሠራላቸው ውለታ እርሷንም እቤቷ ድረስ እየተመላለሰ የጠየቃት ከሁሉም በላይ ደግሞ ለእንዳለ ያላት ጥልቅ ፍቅር አሻፈረኝ ብላ ለመጽናት እንቅፋት ሆነውባት ከራሷ ስትጣላና ሰትስማማ ነው የለነበተችው በወንድሟ አሳማኝ ትንታኔና በራሷም ማገናዘቢያ በእንዳለ ላይ የነበራትን ጥላቻ ያነሳችው ሩቂያ ራሱም ዶክተር አብደላ በፀፀት ተንገብግፀና ተቃጥሎ እንዲያማልዱት ለሚማፀናቸው እንዳለ ጉትጉታ ሳይሆን ሰለ ንጹህ ፍቅር መቃናት የሰብአዊ ስሜታቸውን ግዴታ ለመወጣት ዳርምየለሽን ወጥ ረው ይዘዋታል። ያ ባይሆን ደግሞ የመለያየታቸውን ሚስጥር ተረድቶ ዛሬ በጉጉት ልቡ ተሰቅሎ ለሚጠብቀው አርቅ አይበቃም ነበር ሀብቴ ዝናቡ ለተንኮል ያዘጋጀው መሰናክል ራሱን አደናቅፎት ለእነርሱ ያልታሰበ የመገናኛ ድልድይ ፈጠረሳቸው የተጐዳ ዕለት ሆስፒታል ገብቶ ጥቂት ቀናት ቢቆይም ከዚያ ወጥቶ የት እንደደረሰ አይታወቅም በመሥሪያ ቤትም ሆነ በሠፈር እዚህ ቦታ አየሁት ወይንም እንዲሀ ሆኗል የሚል የለም የሚታወቅ ነገር ቢኖር ከሆስፒታል ሳይወጣ ጉዳዩን ለያዘው መርማሪ ፖሊስ እንዳለን በተጠያቂነት እንደማይፈልገው ቃል መስጠቱና ከሆስፒታል እንደወጣ መጥፋቱ ብቻ ነው ምናልባትም እንዳለን ሊበቀለው ፈልጐ እንዳደፈጠ ወይንም ድርጊቱ አሳፍሮት ወደ ከፍለ ሀገር እንደኮበለለ የተለያዩ የግምት ወሬዎች ይናፈሳሉ ልዩ ልዩ ሞዴልና ስም ያላቸው በርካታ መኪኖች በዓይኖቹ ሥር እንደሚያልፉት ሁሉ ልዩ ልዩ ይዘትና ትዝታ ያላቸው በርካታ ሀሳቦች በህሊናው ሥር እየተመላለሱ ቀሪ ጊዜውን አጫረሱትና ጊዜው ደርሶ የዶክተር አብደላ ፔኙ ብቅ ስትል ሁለመናው አንድ ሆኖ ሰዓቱን አስተዋላትነ ለሩብ ጉዳይ አንድ ደቂቃ ቀርቷታል ፇ ሰሱሞገ ሹምዩ የዛሬ ስንት ዓመት መሆኑ ነው ቀኛዝማች ከፍያለው የእህታቸው የወይዘሮ ጥልፏን የመጀመሪያ ልጅ ተሾመ ማመጫን ከገጠር ያመጡና ከልጆቻቸው ጋር እያስተማሩ ያሳድጉታል እርሱም በትምህርቱ ጐብዞ ሁለተኛ ደረጃ እንደደረስ ከአሥረኛ ክፍል አቋርጦ ራሱን ለመቻል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪነት ይቀጠራል እያስተማረ አንድ ሦስት ዓመት እንደሠራም ራሱን ለመቻል ያለውን ፍላጐት የተረዱት ቀኛዝማች በቅድስት ማርያም ወረድ ብሎ ከነበራቸው ሠፊ ይዞታ መሃል ቤት ያልነበረበትን ከአንድ ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ሰጡትና የእርሳቸው ድጐማ ታክሎበት የራሱን ቤት ሠርቶ በሥራቸው ከመተዳደር ወጣ ሥራ እንደጀመረ ያወቃትንና በኋላም በፍቅር ልቡ ጥፍት ያለላትን ወይዘሪት ለማግባት የቤት ዕቃውን እና አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች በማዘጋጀት ላይ ሳለ እርሱንና ታናሽ እህቱን ያለ አባት ተቸግረው ያሳደጉአቸው እናቱ ሞቱ ከእርሱ የቀረበ ረዳትና አይዞሽ ባይ የሌላት እህቱን ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት ተገደደ በእናቱ ህዘን ምክንያትም የጋብቻ እቅዱን ለአንድ ዓመት አዘግይቶ ከእህቱ ጋር መኖሩን ተያያዘው ያን ጊዜ ብዙነሽ ማመጫ አማርኛዋና ዘርገፍገፍ ያለው እለባበሷ በከተሜ ዓይን ገራገር ከሚያስመስላት በቀር ላያት የምታጓጓ በፍቅር የምትወጋ የአሥራ ስምንት ዓመት ልጃገረድ ነበረች ሊፈነዳ እንደተቃረበ የአበባ እንቡጥ ጥብቅብቅ ብላ ያማረች ገና ከገጠር የመጣች መሆኗን ቢያውቁም እንኳ ስንትና ሰንት ሰለጠንን ባይ ጐረምሶች ያስቸግሯት ነበር አንድ አፍታ ለገበያም ይሁን ቀኛዝማች ከፍ ያለው ቤት ለመሄድ ወጣ ካለች በአድናቆት ፈዝዞ የሚያስተውላት አልፋው ሰትሄድ እየዞረ የሚመለከታት ወይንም በርቀት ዓይኖቹን ጣል አድርጐ የሚከተላት የዓይኑ ሽፋል እስኪረግፍ የሚጠ ቅላት የግንባሩ ሽብሽብ እርጅና እስኪመስልበት ቅንድቡን የሚሰቅልላት ሌላውም ሌላውም የእርምጃዋን ያህል ቁጥሩ በርካታ ነው እንዳላየ ጉኮሳትራና አንገቷን ደፍታ እርሷም በኩራት ትሰልላቸዋለችአዘውትረው ከሚከታተሏትና ከተሳካ ለትዳር ካልሆነም ለፍቅር ከሚመኗት መህል ዳለቻማ ሳሪያን ኮት ከቬል ሱሪ ጋር የሚለብሰው ሪዛሙና ዓይነ ውሃው ሞኛሞኝ የሚመስለው ባህሩ ፍስሀ አንዱ ነበር ከልብሱ በስተተር ነገረ ሥራው ሁሉ የእርሷ ቢጤ ባላገር ስለሚመስላት አንኳንስ ፊት ልትሰጠው ለሙከራውም ያበሽቃት ነበር በኋላ ሳይ ሰማይ መሬቱ ሲደፋባት እና አማራጭ ሲጠፋባት ከነጉዷ ተቀብሎ ከማንም ይልቅ ኣይዞሽ ሊሳት በታላቅ ወንድሟ ማበድ ምክንያት በደረሰባት የመተዳደሪያ ዕጦትና በማህፀኗ በያዘችው እኩይ ፅንስ መዳበር የተነሳ ልትወጣው የማትችለው ችግር ወጥሮ ሲይዛት ነብሳቸውን ይማርና የቀኛዝማች ሚስት ወይዘሮ አይቼሽ ዘንድ ሄዳ በሴት ልጆቻቸው እየተማፀነች አለቀሰችባቸው እርሳቸውም አባብለውና አጽናንተው እህልና ገንዘብ ከደጎሟት በኋሳ ጠሳ እየሸጠች ለዘለቄታው ራሷን እንድትረዳ አማከሯት አቋቋሟትም ያን ጊዜ ነው እንግዲህ ጣሳ ሰው አይመርጥምና ባህሩ ፍሰሃ በገዛ ቤቷ ስተት ማለት የጀመረው ጠላ የለም ወይንም አለቀ ካልተባለ በስተቀር በቀን ሁለት ሦስት ጊዜ ተመላልሶ ይመጣል አንዳንዴ ሂሳብ ሲከፍል ከጠጣበት በላይ የሚሆን መልስ ያለፍላጐቷ ትቶላት ይሄዳል።